Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ችግር ፈቺ የሆኑ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ተገኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓን አፍሪካ ዩኒቨርስቲ በውሃ፣ በምግብ ኢነርጂ፣ በአየር ጸባይ ለውጥ፣ በመልካም አስተዳደርና በሰው ሀብት ልማት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች አፍሪካዊ የሆኑ ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ የፈጠራና የምርምር ውጤቶች መገኘታቸው ተገለጸ።

በአፍሪካ ሕብረት የትምህርት፣ ሳይንስና፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ሞሀመድ ቤልሆሲን በዚህ ወቅት በሰጡት መግለጫ ፥ በአሁኑ ወቅት በፓን አፍሪካ ዩኒቨርስቲ ስር ባሉ ተቋማት በኩል በአምስት የተለያዩ የአፍሪካ ክፍሎች ማለትም በአልጄሪያ፣ ኬኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ካሜሮን እና ደቡብ አፍሪካ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።

“በእነዚህ ተቋማት የውሃ፣ ኢነርጂ፣ በአየር ጸባይ ለውጥ፣ በመልካም አስተዳደርና በሰው ሃብት ልማት ፣ በግብርና መሬት ጥናት ጉዳዮች ላይ ምርምሮችን ጨምሮ አፍሪካዊ የሆኑ የስራ ፈጠራዎች፣ አዳዲስ ግኝቶችና የስነ ምግብ ውጤቶች ተገኝተዋል’’ ነው ያሉት።

ፕሮፌሰር ሞሀመድ ቤልሆሲን አክለውም ፥ ኮሚሽኑ የትምህርት ጥራትን፣ ተደራሽነትንና ቴክኖሎጂያዊ ስኬቶችን ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተለይም የፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ጽንሰ ሀሳብ ከተጠነሰሰበት እ.አ.አ ከ2008 ጀምሮ ትምህርትን በከፍተኛ ጥራት የሚሰጡ፣ በቴክኖሎጂ የታገዙ እና ስራ እድል ፈጠራን የሚያግዙ ተቋማትን ለማቋቋም እየሰራ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል በአፍሪካ ሕብረት 2063 አጀንዳ መነሻነት የኤሌክትሮኒክስ ትምህርት በርቀት የሚሰጥብት የፓን አፍሪካን ኤሌክትሪካል እና ቨርቹዋል ዩኒቨርስቲ መመስረቱን ተናግረው፤ በየትኛውም ክፍል የሚገኙ አፍሪካውያን ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ሲሉም ነው የተናገሩት።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version