Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለአማራ ክልል የ14 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን በአማራ ክልል በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ ንብረቶች መልሶ ለመገንባት የሚውል የ14 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

አሸባሪው ቡድን በወረራ ይዟቸው በነበሩ የአማራ ክልል አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የፌዴራል ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ከኢትዮጵያ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ ከኢትዮጵያ ሲሚንቶ ፋብሪካ ማህበራት ጋር በመሆን 10 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብና 4 ሚሊየን ብር በዓይነት አስረክቧል።

ድጋፋን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ዶክጸር ይልቃል ከፋለ ማሽረከባቻን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version