Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጋምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቢያ ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢሳቱ ቶራይ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቷና የልዑካን ቡድናቸው ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ፤ የውጭጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version