አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የአገር መከላከያ ተቋም በጦርነት ተጠምዶ ቢቆይም ጎን ለጎን በርካታ የልማት ስራዎችን አከናውኗል” ሲሉ የአገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ።
ተጠሪነታቸው ለመከላከያ ሚኒስቴር የሆኑ ክፍሎች የ2014 ዓ.ም የ6 ወር እና የመቶ ቀን የስራ አፈፃፀም ግምገማ የተካሄደ ሲሆን ÷የአገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሀም በላይ እና ሌሎች የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ዶክተር አብርሃም በላይ ÷ተቋሙ አብዛኛውን ጊዜውን በጦርነት ተጠምዶ ያሳለፈ ቢሆንም ከጦርነቱ ጎን ለጎን መልካም የሚባሉ ተቋማዊ የልማት ስራዎችን ሰርቷል ብለዋል።
ወደፊትም ጠላቶችን በማሳፈር የኢትዮጵያን ሰላም በማስጠበቅ እና ተቋሙን ወደ ተሻለ የእድገት ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ ገልጸዋል።
“በዚህ ረገድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ስራ ለመስራት የቴክኖሎጅ ውጤቶችን በመጠቀም ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት ጠንክረን እንሰራለን” ብለዋል።
በግምገማው ላይ የተቋሙ የወደፊት አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ÷አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ይልቅ የተጀመሩትን ማጠናቀቅ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

