Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ የፕሮጀክት ስራዎችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ገላን ከተማ የሚገኙ የዶሮ እርባታና የብሎኬት ማምረቻ ፕሮጀክቶችን ጎበኘ፡፡
ልዑኩ የጎበኘው የብሎኬት ማምረቻ በአርሶ አደር ነጋሽ ዳቢ ኢንቨስት የተደረገ ሲሆን÷ ለ35 ሴቶች እና ለ15 ወንዶች ወጣቶች የስራ ዕድል የፈጠረ ነው ተብሏል፡፡
በአካባቢው የአርሶ አደሮችን የግብርና ስራ እንቅስቃሴም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በተመሳሳይ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 8 ሜትር ስፋት ያለው በ90 ሚሊየን ብር ወጭ በአቶ አደም ከድር የተገነባ የአስፋልት መንገድም የጉብኝቱ መዳረሻ ሆኗል፡፡
የልዑካን ቡድኑ የሜልባ ፕሪንቲንግ ፐብሊሺንግና ፖኬጂንግ አ.ማ እንዲሁም የሆራ ኮኦፕሬቲቭ ግሩብ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን ጎብኝቷል።
በሌላ በኩል አፍሪካ ነዳጅ ማካፋፈያ እና የአዳማ ቆርቆሮ ፋብሪካ ገላን ቅርንጫፍ ርዕሰ መስተዳድሩ መርቀው ከፍተዋል፡፡
በሌሊሴ ተስፋዬ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version