Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዳያስፖራው ያሰባሰበውን 20 ሚሊየን ብር የሚገመት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው ‘በአይዞን ኢትዮጵያ’ መተግበሪያ ያሰባሰበውን 20 ሚሊየን ብር የሚገመት ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።

የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር መሃመድ ሁሴን፥ ድጋፉን በመረከብ ለተደረገው ለልግስናው ምስጋና አቅርበዋል።

የተደረገው ድጋፍ በክልሉ አሸባሪው ህውሓት በከፈተው ጦርነት ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ትልቅ እገዛ እንደሚሆን ተናግረዋል።

የተደረገው ድጋፍም ከ200 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች እንደሚውል ኢዜአ ዘግቧል።

በዚሁ መተግበሪያ ከተሰባሰበው ገንዘብ ለአማራ ክልል በቀጣይነት ተመሳሳይ ድጋፍ እንደሚደረግም ተገልጿል።

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት በሰሜን ሸዋዞን ለሚገኘው መዘዞ ጤና ጣቢያ 1 ሚሊየን ብር የሚጠጋ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ጤና ጣቢያው በተደረገለት ድጋፍ መሰረታዊ የህክምና አገልግልቶችን እንደጀመረ የጤና ጣቢያው ሀላፊ ሚሊዮን ደመረ ለፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በአላዩ ገረመው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version