Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደብረ ማርቆስ ከተማ የተገነባው የግራናይት ፋብሪካ የሙከራ ምርት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ማርቆስ ከተማ የተገነባው የግራናይት ፋብሪካ የሙከራ ምርት ማምረት ጀመረ።
 
በፋብሪካው የሙከራ ምርቱ ጅማሮ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
 
በአያልነህ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተገነባው “እቴ የግራናይት ፋብሪካ” ለግንባታ ስራው 360 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት መሆኑ ተገልጿል።
 
ክልሉ ያለውን ሰፊ የግራናይት ሀብት ጥቅም ላይ ለማዋል የተገነባው ይህ ፋብሪካ፥ ከውጪ የሚገባውን የግራናይት ምርት ከማስቀረትና የውጭ ምንዛሬን ለማዳን አንፃር ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው አሚኮ ዘግቧል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version