Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ያሻል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንደሚያሻ የቱርክ ፕሬዚዳንት ቃል አቀባይ ኢብራሂም ካሊን ገለጹ፡፡

የኔቶ አባል ሀገር የሆነችው ቱርክ ከሩሲያ እና ዩክሬን ጋር መልካም ግንኙነት እንዳላት ቃል አቀባዩ የተናገሩ ሲሆን፥ ቱርክ በሁለቱ ሀገራት የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ የሚጠበቅባትን ገንቢ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች ብለዋል፡፡

ኢብራሂም ካሊን ÷ ሩሲያ የወሰደችው የቅርብ ጊዜ እርምጃ ዩክሬንን ከመያዝ ይልቅ ከአሜሪካ እና ከኔቶ ጋር ተደራድራ የቀጠናውን ሠላም ለማስጠበቅ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡

ሩሲያ በቅርቡ በዩክሬን አቅራቢያ ከ100 ሺህ በላይ ወታደሮቿን ማስጠጋቷን ተከትሎ ወታደራዊ ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች የሚል ስጋት በኔቶ በኩል ተፈጥሯል፡፡

ሩሲያ በበኩሏ ዩክሬንን የመውረር እቅድ የለኝም፤ ወታደሮቼም ለልምምድ ነው የተሰባሰቡት ማለቷን አናዶሉ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version