Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው ህወሓት ከ 1 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት እንደደረሰበት ገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በፈጸመው ውድመትና ዘረፋ ምክንያት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ሃብትና ንብረት አጥቻለሁ ሲል በጥናት ማረጋገጡን አስታወቀ፡፡

 

የዩኒቨርሲቲው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ እድሪስ ይማም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ወራሪው ቡድን ከ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ሃብትና ንብረት አውድሟል፡፡

 

ዩኒቨርሲቲው ከደረሰበት ከፍተኛ ውድመት በአጭር ጊዜ አገግሞ ሀገራዊ ተልዕኮውን እንዲወጣ የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የግብዓት ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ገልጿል።

የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን አጠቃላይ ግምቱ ከ1 ሚሊየን 720 ሺህ ብር በላይ የሆነ የተለያዩ ግብዓቶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ልዑክ በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ቱሉ አውሊያ ካምፓስ ተገኝቶ አስረክቧል፡፡

በተመሳሳይ የደባርቅ፣ ኦዳ ቡልቱም፣ ወልቂጤ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን አቶ እንድሪስ ይማም ገልጸዋል፡፡

ድጋፍ ላደረጉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ላስተባበሩ አካላት መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ምስጋና አቅርቧል።

 

በሰላም አሰፋ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version