Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንትና የተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ በሽብር ቡድኑ ጉዳት የደረሰባቸውን ህፃናት ጠየቁ

አዲስ አበባ፣የካቲት 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን ህፃናት ዱብቲ ሆስፒታል በመገኘት ጠየቁ።

ህፃናቱ ጉዳት የደረሰባቸው የሽብር ቡድኑ በተኮሰው ከባድ መሳሪያ መሆኑ ተገልፆላቸዋል።

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንትና የተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ በተጨማሪም በሠመራ ከተማ የሚገኘውን የአለም ምግብ ድርጅት መጠባበቂያ መጋዘን የምግብ ክምችት መመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version