Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዱባይ ኤክስፖ በኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዱባይ ኤክስፖ 2020 በኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ ላይ ያተኮረ ፎረም ተካሄደ፡፡

በመድረኩ የተሳተፉት የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ ለሊሴ ነሜ፥ በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍን ማዕከል አድርጎ የተካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም ውጤታማ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እምቅ አቅም እንዳላት ማስተዋወቅ ችለናል ያሉት ኮሚሽነሯ፥ ትልልቅ ኩባንያዎች በሀገሪቱ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት ማሳየታቸውን ተናግረዋል፡፡

በተለያዩ ሴክተሮች መሰል ፎረሞች እንደሚኖሩ ጠቁመው፥ ኢትዮጵያን ሊቀይሩ የሚችሉ ኢንቨስትመንቶች ይመጣሉ ብለን እናስባለን ብለዋል፡፡

በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በበኩላቸው ፎረሙ በኢትዮጵያ ያለው መልካም የንግድና የኢቨስትመንት እድሎች ለኤክስፖ 2020 ለመጡ እንዲሁም ለተባበሩት አረብ ኤሜሬት ባለሃብቶች የተዋወቀበት ነው ብለዋል፡፡

ይህም የተሳካ ነበር ያሉት አምባሳደሩ፥ በመድረኩም በርካታ ባለሃብቶች መገኘታቸውንና በኢትዮጵያ መዋለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት ማሳየታቸውን ገልጸዋል።

ባለሃብቶቹ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ያለውን የንግድና የኢቨስትመንት እድሎች በማየት ወደ ተግባር ለመግባት ቃል መግባታቸውንም ነው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ የሚያመለክተው፡፡

በፌቨን ቢሻው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version