አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ግሎባል አሊያንስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በ10 ሚሊየን ብር ወጪ በአፋር ክልል ሎጊያ ከተማ የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ሊያካሄድ መሆኑ ተገለጸ።
ድርጅቱ በሎጊያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የማስፋፊያ ግንባታ ለመጀመር የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጧል።
እስከ 7ኛ ክፍል ድረስ የሚያስተምረው የሎጊያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ወይዘሮ ህይወት ሽመልስ በስነሰርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ፥ ትምህርት ቤቱ በአንድ ክፍል እስከ 120 ተማሪዎች በተጨናነቀ ሁኔታ እያስተማረ ይገኛል።
ትምህርት ቤቱ የመማሪያና አስተዳደር ክፍሎች ጥበት በተጨማሪ የውሃና የመጸዳጀ ቤት ችግሮች ያሉበት መሆኑን ጠቁመው ፥ ችግሩ ተማሪ የመቀበል አቅሙን እንደገደበበት ገልጸዋል።
ትምህርት ቤቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ትውልድ ለመቅረጽ የሚያደርገው ጥረት የሚበረታታ ነው ያለው የግሎባል አሊያንስ ቦርድ ሰብሳቢ አርቲስት ታማኝ በየነ ፥ የትምህርት ቤቱን ችግሮች ለመፍታት የድርጅቱን አባላት በማስተባበር በቀጣይ ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግሯል።
ግንባታው እስከ 10 ሚሊየን ብር ወጪ እንደሚፈጅና ስራው በአፋር ልማት ማህበር በኩል የሚከናወን መሆኑን የኢዜአ ዘገባ ያመልከታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

