አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጋምቤላ ከተማ በ79 ሚሊየን ብር ለሚያስገነባው የኢፈ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጡት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ናቸው።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ በወቅቱ እንዳሉት ፥ ትምህርት ቤቱን መገንባት ያስፈለገው የሁለቱን ክልል ህዝቦች የትምህርት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ነው።
በኦሮሚያና ጋምቤላ ክልሎች መካከል ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ በልማት የሚደረግ ትብብር እየተጠናከረ መጥቷል” ያሉት ደግሞ የጋምቤላ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ናቸው።
የኦሮሚያ ክልል በጋምቤላ ከተማ ለሚያስገነባው ትምህርት ቤት ምስጋና አቅርበዋል።
የትምህርት ቤቱ ግንባታ በስምንት ወራት ውስጥ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ በመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጥ ስነ ስርዓቱ ላይ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

