Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ወላይታ ዲቻ 3ኛ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ወላይታ ዲቻ መከላከያን በማሸነፍ 3ኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል፡፡

በ12ኛው የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ወላይታ ዲቻ መከላከያን 1 ለ 0 በማሸነፍ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል፡፡

አንተነህ ጉግሳ የወላይታ ዲቻን የማሸነፊያ ጎል በ7ኛው ደቂቃ ላይ አስቆትሯል፡፡

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቀጥለው ሲካሄዱ አርባ ምንጭ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ትላንት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና አዲስ አበባ ከተማን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ባህርዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version