Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ከ110 ሚሊየን በላይ የአበባ ዘንግ ወደተለያዩ ሀገራት አጓጓዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ባለፉት ሁለት ሳምንታት 86 በረራዎችን በማድረግ ከ110 ሚሊየን በላይ የአበባ ዘንግ ወደተለያዩ ሀገራት ማጓጓዙን አስታወቀ።

እንደ ዓየር መንገዱ ገለፃ የአበባ ዘንጎቹን በዋናነት ከኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ ሀገራት ቢያጓጉዝም፥ በተጨማሪም ምርቱን ከኬንያ፣ ኢኳዶር፣ ኮሎምቢያና ሚያሚ (ዩናይትድ ስቴትስ) ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት አጓጉዟል።

አየር መንገዱ “የፍቅረኞች ቀን” (የቫለንታይን ደይ) በሚውልበት በዚህ ወር የሙቀት መቆጣጠሪያ በተገጠመላቸው ዘመናዊ እቃ ጫኝ አውሮፕላኖቹ ነው የአበባ ምርቶችን ወደተለያዩ የዓለም ሀገራት በማጓጓዝ ላይ የሚገኘው።

በመላው ዓለም የፍቅረኞች ቀን በሚውልበት በያዝነው የፈረንጆቹ ወር የአበባ ገበያ እጅጉን ይደራል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version