አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 7 ወራት ውስጥ 196 ቢሊየን 798 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገቢው በርካታ ተግዳሮቶችን በማለፍ መሰብሰቡን ጠቁመዋል።
በዚህም በተጠቀሱት ወራት ለመሰብሰብ ከታቀደው 92 ነጥብ 45 በመቶውን ማሳካት ተችሏል ነው ያሉት፡፡
ገቢው ከ2013 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነፃፀር የ27 ቢሊየን 430 ሚሊየን ብር ወይም 16 ነጥብ 2 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን አንስተዋል፡፡
የተገኘው ገቢ ከሀገር ውስጥ ታክስ እና ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ የተሰበሰበ መሆኑን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡
የተሰበሰበው ገቢ በአገሪቱ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት አራት የተቋሙ ቅርንጫፎች ከሥራ ውጭ ሆነው፣ ከኮሮና ወረርሽኝ እና መሰል ተጨማሪ ችግሮች አንፃር ሲታይ ጥሩ አፈጻጸም መሆኑን አውስተዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!