አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በነዳጅ አቅርቦትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
ውይይቱ ከነዳጅ ግብይት ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማ ሰሞኑን ለተፈጠረው ችግር የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እና በቀጣይ የነዳጅ ግብይቱ በስርዓት እንዲመራ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሰነዱ ላይ ውይይት መደረጉ በዘርፉ እየታዩ ያሉ ዋና ዋና ማነቆዎች በዝርዝር በመለየት የከተማዋን ማህበረሰብ ተጠቀሚነት ማረጋገጥ ያስችላል ተብሎ እንደሚጠበቅ በሰነዱ ላይ ተጠቁሟል፡፡
በአዲሱ ሙሉነህ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

