Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጌዴኦ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በቆንጋ ቀበሌ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው ከያቤሎ ወደ ሻሸመኔ 45 ሰው ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በመገልበጡ የደረሰ ነው፡፡

በዚህም የ6 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ አደጋ ማድረሱን የይርጋጨፌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ታምራት ምትኩ ገልጸዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በይርጋጨፌና በዲላ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን፥ የአደጋ መንስኤው እየተጣራ መሆኑን ከዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version