Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደሴ ከተማን ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት የደሴ ከተማን ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት ከ16 ሚሊየን ብር በላይ መድቦ እየሰራ መሆኑን የከተማዋ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ።
በመምሪያው የኢንስፔክሽን ቡድን መሪ አቶ ይማም ሰይድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ከመንግሥት በመመደብ ያጋጠመውን የኑሮ ውድነት ለማሻሻልና መሠረታዊ ፍላጓቶችን ለማማሟላት እየተሠራ ነው።
በዚህም ከ3 ሺህ ኩንታል በላይ ጤፍ እና ከ800 ኩንታል በላይ ዱቄት በሸማች ማኅበራት እንዲቀርቡ ማድረግ መቻሉንም ነው የተናገሩት፡፡
ወደፊትም ወሳኝ የሚባሉ መሠረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን ለማህበረሰቡ ለማቅረብ እንደሚሰራ አቶ ይማም ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በከተማዋ የሚታየውን ህገ ወጥ ንግድ ለመቆጣጠር እቅድ ተይዞ ወደ ተግባር መገባቱንም ነው መምሪያው የገለጸው፡፡
መምሪያውን ጨምሮ 10 ማዕከላትን ወደ ሥራ በማስገባት ህገ ወጥ የቡና ንግድ፣ የጎዳና ላይ ንግድና ያለንግድ ፈቃድ የሚሰሩ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ንግድ ፈቃድ ባላደሱና ንግድ ፈቃድ በሌላቸው ነጋዴዎች ላይም ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የገለጹት አቶ ይማም÷ ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በከድር መሀመድ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version