አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ገምግሞ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ለስድስት አንጋፋና ወጣት ተመራማሪዎች የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታወቀ፡፡
የዩኒቨርሲቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አለምእሸት ተሾመ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ የዩኒቨርሲቲ ው አስተዳደር ቦርድ ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ገምግሞ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ለስድስት አንጋፋና ወጣት ተመራማሪዎቹ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡
በዚህም መሰረት ለዶክተር ማሽላ ደጀኔ ወልደሚካኤል በዕፅዋት በሽታ ጥናት “ፕላንት ፓቶሎጂ”፣ ለዶክተር ዋሱ መሐመድ አሊ በዕፅዋት ዝርያ ማሻሻል “ፕላንት ብሪዲንግ” እና ለዶክተር ንጉሴ ቡሳ ፌዳሳ በ”ባዮኬሚስትሪ እና ፊዚዮሎጂ” የሙሉ ፕሮፈሴርነት ማዕረግ እንደተሰጠ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ለዶክተር አቢ ታደሰ በ”ኢንኦርጋኒክ ኬሚስትሪ”፣ ለዶክተር ምትኩ እሸቱ ጉያ በእንስሳት እርባታ እና ለዶክተር ተስፋሕይወት ዘሪሁን በቨተርነሪ ክሊኒካል ፓቶሎጂ (ስነ ደዌ) የሙሉ ፕሮፈሴርነት ማዕረግ ሰጥቷል።
ተመራማሪዎቹ ባከናወኗቸው የምርምር ስራዎች፣ በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ የህትመት ውጤቶችን በማሣተማቸውና በማህበረሰብ አገልግሎት ባበረከቱት አስተዋፅዖ የሙሉ ፕሮፌስርነት ማዕረጉ እንደተሰጣቸው ተገልጿል።
በተሾመ ኃይሉ ተጨማሪ መረጃ ከዩኒቨርሲቲው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

