ምክር ቤቱ ዛሬ እያካሄደ ባለው ልዩ ስብሰባ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ይሾማል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ በሚገኘው ልዩ ስብሰባ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ይሾማል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛ ልዩ ስብሰባው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265 /2014 ማጽደቁ ይታወቃል፡፡
ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ ማህበረሰቡ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነሮችን እንዲጠቁም በማድረግ ከ600 በላይ ዕጩ ኮሚሽነሮች መጠቆማቸውን ይፋ አድርጓል፡፡
ከእነዚህ ውስጥም ምክር ቤቱ ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነር ይሆናሉ ያላቸውን 42 ግለሰቦች ህብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ዝርዝራቸውን ይፋ ማድረጉም ይታወሳል፡፡
ምክር ቤቱ ከማህበረሰቡ የተገኘውን ግብዓት ከተመለከተ በኋላም መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ አሟልተዋል ያላቸውን እጩ ኮሚሽነሮች በመምረጥ እንዲሾሙ ለምክር ቤቱ አቅርቧል፡፡
በዚህ መሰረትም ፡-
1. ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ – ሰብሳቢ
2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ – ምክትል ሰብሳቢ
3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ
4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሃመድ
5. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድህን
6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ
7. አቶ ዘገየ አስፋው
8. አቶ መላኩ ወልደማሪያም
9. አምባሳደር መሃሙድ ድሪር
10. አቶ ሙሉጌታ አጎ እና
11. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ እጩ ኮሚሽነር ሆነው ቀርበዋል፡፡
ምክር ቤቱ ዛሬ እያካሄደው በሚገኘው ልዩ ስብሰባ በእነዚህ እጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከተወያየ በኋላ ይሾማቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በሃይለየሱስ ስዩም

