Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነትና መሰል የህዝብ ጥያቄዎችን መከታተል የምክር ቤቶች ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኑሮ ውድነቱን ጨምሮ ህዝቡ የሚያነሳቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች ምክር ቤቱ ሃላፊነት ወስዶ ምላሽ እንዲሰጥባቸው እንዲከታተሉ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ አሳሰቡ።

የአማራ ክልል ምክር ቤት እና በስሩ የሚገኙ ምክር ቤቶች የ6 ወር የሥራ አፈጻጸም ግምገማቸውን በኮምቦልቻ ከተማ እያካሄዱ ነው፡፡

አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ምክር ቤቱ የግብርና ግብአቶች ስርጭትና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት የማረጋገጥና የመከታተል ሃላፊነት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

ተፈናቃዮችን በዘላቂነት የማቋቋም ፣ የአገልግልት አሰጣጥን የመከታተልና በወራሪው ሃይል የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ የመገንባት ተግባራትን የመገምገም ሃላፊነትም የምክር ቤቱ መሆኑ ተነስቷል።

አሁንም ወራሪው ኃይል ከክልሉ ስላልወጣና ጸብ አጫሪ ድርጊቶችን እየፈጸመ ስለሆነ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት እንዲሰሩም አፈ-ጉባዔዋ አሳስበዋል፡፡

በስንታየሁ መሀመድ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version