Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል በሚገኙ የውሀ ተቋማት ላይ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ውድመት አድርሷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ ክልል በሚገኙ የውሀ ተቋማት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ውድመት ቢያደርስም የገጠመን ችግር ከእኛ አቅም በታች ስለሆነ በመተባበር እና አንድ በመሆን እንሻገረዋለን ሲሉ የአማራ ክልል ውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው ተናገሩ፡፡
የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ ከሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ዞኖች መምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም ከወረዳ ጽህፈት ቤት ባለድርሻዎች ጋር በኮምቦልቻ ከተማ እየተወያዩ ነው፡፡
በውይይቱም ወራሪው ኀይል በአማራ ክልል በሚገኙ የውኃ ተቋማት ላይ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ውድመት ማድረሱ ተገልጿል፡፡
በከተሞች ብቻ 102 የሚደርሱ የውኃ ተቋማት ውድመት የደረሰባቸው ቢሆንም÷ በመንግሥት እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ርብርብ አብዛኞቹ ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል ነው የተባለው።
ጉዳት የደረሰባቸው የገጠር የውኃ ተቋማት ወደ ነበረ አገልግሎታቸው ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ እና ለዚህም ክልሉ በርካታ ፓምፖች እና ተጨማሪ ግብአቶችን ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ በውይይቱ ተነስቷል፡፡
በመድረኩ የክልሉ ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ ለወረዳ ውኃ ጽህፈት ቤቶች ከ4ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የተለያየ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉም ተመላክቷል፡፡
በዘሩ ከፈለኝ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version