Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዓለም ጤና ድርጅት ለሶማሌ ክልል 50 ሜትሪክ ቶን የህክምና ግብዓቶች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት ለሶማሌ ክልል 50 ሜትሪክ ቶን መድኃኒቶችን፣ የህክምና ቁሳቁሶችን እና የአልሚ ምግቦችን ድጋፍ አደረገ።

ድርጅቱ በትዊተር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ድጋፉን በጎዴ እና ጅግጅጋ ከተማ በድርቅ እና በተለያዩ በሽታዎች የተጎዱ በሚሊየን ለሚቆጠሩ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግና በክልሉ የጨቅላ ሕፃናት የአልሚ ምግብ ፍላጎትን ለማሟላት የሚውል ነው ብሏል።

ያቀረበው የመድኃኒት ድጋፍም ባለፈው ወር ለክልሉ ከተላለፈው የሕክምና ቁሳቁስ በተጨማሪ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት የሚታገዝ የጤና ሚኒስቴር እና ግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ ልዑክ በክልሉ ሸበሌ ዞን ምልከታ አድርጓል።

ድርጅቱ እንዳለውም ምልከታው የኢትዮጵያ መንግሥት እና በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በክልሉ ለተከሰተው ድርቅ ምላሽ ለመስጠት ያላቸውን ቁርጠኝነት ያረጋገጠ ነው።

በኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት የክትትል እና ፈጣን ምላሽ፣ ሥነ ምግብ፣ የውሃ፣ የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና አጠባበቅ (ዋሽ)፣ የክትባት እና የሎጂስቲክስ ባለሙያዎች በክልሉ ለተከሰተው ድርቅ ለሚሰጠው ምላሽ ቀጥተኛ የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉም ብሏል ድርጅቱ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version