አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በስምንት ወራት ውስጥ 250 ኩንታል የሀሺሽ ምርት ማስወገዱን የምዕራብ አርሲ ዞን ፀጥታና አስተዳደር አስታወቀ።
በገጠር ገበሬ ማኅበር እና በከተማ ውስጥ በየጥሻው በስፋት የሚመረተው የሀሺሽ ምርት የሽያጭ ሰንሰለቱ እስከ ኬንያ ድረስ መሆኑን የገለጸው የምዕራብ አርሲ ዞን፥ በስምንት ወራት ውስጥ 250 ኩንታል የሀሺሽ ምርት በማቃጠል ማስወገዱን አስታውቋል።
የምዕራብ አርሲ ዞን ፀጥታና አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ ኮማንደር ጌታቸው ታዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ባለፈው ዓመት ሀሺሽ በብዛት ይመረትባቸው ከነበሩ አራት የዞኑ ወረዳዎች ውስጥ ሦስቱ ነጻ እንዲሆኑ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
አሁንም በሻላ ወረዳ ምርቱ በስፋት በማሳ ደረጃ እየተመረተ እንደሆነና አካባቢውን ከሀሺሽ ነፃ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
የሀሺሽ ምርትን አርሶ አደሩ እንደ ገቢ ምንጭነት እየተጠቀመው ነው ያሉት ኮማንደር ጌታቸው፥ በወንጀል ድርጊቱ የተያዙ ግለሰቦች ላይ የሚወሰደው እርምጃ እና የህግ ተጠያቂነት መላላት የቁጥጥር ሥራውን ውጤታማ እንዳይሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡
ይህንን ችግር ለመፍታትም በቀጣይ ከፍርድ ቤትና አቃቤ ህግ ጋር የሚሰራ ይሆናልም ነው ያሉት ብለዋል።
በመቅደስ አስፋው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

