Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የህዳሴ ግድቡ ኃይል ማመንጨት መጀመር ከፍተኛ ስትራቴጂያዊ ፋይዳ አለው- አምባሳደር መለስ ዓለም

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ከፍተኛ ስትራቴጂያዊ ፋይዳ እንዳለው እና የኢትዮጵያንና የኬንያን ኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር እንደሚያጠናክር በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም ተናገሩ።

በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል የኃይል ግዢ ስምምነትን የሚከታተል የቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ በናይሮቢ ከተማ የተካሄደ ሲሆን÷ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ለአካባቢው ሀገራትና ለተቀረው ዓለም ስትራቴጂያዊ ፋይዳ እንዳለው አምባሳደር መለስ አስረድተዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በመሪዎችም ሆነ በሕዝብ ደረጃ የቀየና ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው÷ ለረጅም ጊዜ የቆየውን ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚያስችል ነውም ብለዋል።

ሀገራቱ ረጅም እድሜ ያስቆጠረ ጠንካራ ወዳጅነት እንዳላቸው ጠቅሰው፥ ኢትዮጵያ ይህ ግንኙነታቸው በተለያዩ መስኮች ጎልቶ እንዲቀጥል ቁርጠኛ መሆኗን አብራርተዋል።

የህዝቦችን የልማት እቅድ ጉዞ ለማሳካት ኮሚቴው የኃይል ግዥ ስምምነት ፕሮጀክቱን በፍጥነት እውን እንዲያደርግ እና እንዲከታተል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፕሮጀክቱን ለፍሬ ማብቃት እንደሚገባም የተገለጸ ሲሆን÷ በኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኃይል ዘርፍ ዋና ፀሐፊ ጎርደን ኪሃላንግዋ ሁለቱ ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version