አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሀገር ውስጥ ለሚገኙ አምራች ባለሐብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እያስጎበኘ ይገኛል።
ጥሪ የተደረገላቸው ባለሐብቶች እና የኩባንያ ተወካዮች በቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን ፥ በፓርኮቹ ውስጥ ስላሉ የአምራች ዘርፎች እና መሠረተ ልማቶች እንዲሁም አገልግሎት አሠጣጥና ድጋፎች የተመለከተ ገለጻ እየተደረገላቸው እንደሆነ ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

