አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢድ አልፈጥር እና ሸዋል ኢድ በዓላትን ለማክበር ወደ ሐረሪ ክልል የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል እና ለማስተናገድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ክልሉ አስታወቀ፡፡
የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሔኖክ ሙሉነህ÷ እንግዶችን ለመቀበልና ለማስተናገድ ግብረ-ሃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ መገባቱን ጠቁመው፥ ለዚህም ሆቴሎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንግዶችን ለማስተናገድ ከመንግስት እና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመቀናጀት መስራት ጀምረዋል።
በክልሉ ያሉትን የቱሪስት መዳረሻዎች ለጎብኚዎች ምቹ በማድረግ በቱሪዝም ዘርፍ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና ቱሪዝሙን ለማነቃቃት እየተሠራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
እንግዶቹ በክልሉ በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሠራ ነው መባሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተለያዩ ዓለማት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ኢድ አልፈጥር እና ሸዋል ኢድ በዓል በሀገራቸው እንዲያከብሩ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

