አዲስ አበባ፣ የካቲት 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች መዳረሻ ለማድረግ ሰፊ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ፡፡
በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት፣ ንግድ እና ቱሪዝም ላይ ያሉ እድሎችንና ተሞክሮዎችን ለውጭ ባለሃብቶች ማስገንዘቢያ የፓናል ውይይት በዱባይ ተካሂዷል፡፡
በመርሃ ግብሩም የንግድ፣ ቱሪዝም፣ የባህልና ስፖርት እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የስራ ሃኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ ከተለያዩ ዓለማት የመጡ ባለሃብቶች፣ ኩባንያዎች እና በኢትዮጵያ ቀደም ሲል በኢንቨስትመንት የተሰማሩ የውጭ ሀገራት ባለሃብቶችም ተሳትፈዋል። ባለሃብቶቹም በዱባይ ኤክስፖ 2020 የኢትዮጵያን እልፍኝ የጎበኙና በቀጣይ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ፍላጎት ያሳዩ መሆናቸው ተገልጿል።
በመድረኩ መንግስት በሀገር ውስጥ ያለውን የኢንቨስትመንት ስራዎችን በፖሊሲ፣ ስትራቴጅ እና የመሰረተ ልማት ዝግጁነትና አጠቃላይ አስቻይ መደላድሎችን፣ በሃገር በቀል ኢኮኖሚ እሳቤ የተተገበሩ እና ቀጣይ የታቀዱ ትልሞች ለታዳሚዎች እና ለባለሃብቶች ገለጻ ተደርጓል።
በሀገር ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች በኢንቨስትመንት የተሳተፉ የውጭ ሀገራት ባለሃብቶች ተሞክሯቸውን አካፍለዋል።
በፍሬህይወት ሰፊው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

