Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ትውልዱ አንድነት ሃይል መሆኑን ከቀደምት አባቶቹ ተምሮ የተሻለች ኢትዮጵያን ለልጆቹ ማውረስ ይኖርበታል – የሀረሪ ክልል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሁን ያለው ትውልድ አንድነት ሃይል መሆኑን ከቀደምት አባቶቹ ተምሮ የተሻለች ኢትዮጵያን ለልጆቹ ማውረስ ይኖርበታል ሲል የሀረሪ ክልል ገለፀ፡፡

ክልሉ ለ126ኛው ዐድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልክት አስተላለፏል፡፡

ክልሉ በእንኳን አደረሳችሁ መልክቱ ዐድዋ የኢትዮጵያውያን የጀግንነት፣ የአልገዛም ባይነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን አመላክቷል።

ኢትዮጵያውያን በዐድዋ የቅኝ ገዢዎችን እብሪት በመስበር በመላው ዓለም ላሉ ብሎም ለአፍሪካውያን ቀኝ ተገዢዎች የይቻላል ስሜትን መፍጠራቸውንም አስታውሷል።

ለዚህ ታላቅ ድል መመዝገብ ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው በአንድነት በመቆማቸውም የተመዘገበ ገድል ስለመሆኑም አመላክቷል።

የዘንድሮ ዐድዋ ድል በዓል መላው ኢትዮጵያውያን በሽብርተኛ ቡድኖች የተከፈተባቸውን ጥቃት አንድ ሆነው ከመከቱ በኋላ መከበሩ ለየት እንደሚያደርገውም ጠቅሷል።

ከዚህ ባለፈም በህዝብ ተሳትፎ እየተገነባ የሚገኘው የህዳሴ ግድብ ሃይል ማመንጨት በጀመረበት ማግስት መከበሩ የበዓሉን ደስታ እጥፍ ድርብ እንደሚያደርገውም ጠቁሟል።

አሁን ያለው ትውልድም አንድነት ሃይል መሆኑን ከቀደምት አባቶቹ ተምሮ የተሻለች ኢትዮጵያን ለልጆቹ ማውረስ ይኖርበታል ማለቱን ከክልሉ መግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version