Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የገቢዎች ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 34 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን በድርቁ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሆን 34 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።

ድጋፉን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች ለሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ አስረክበዋል።

ድጋፉም በኮንትሮባንድ የተያዘ 22 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚገመት የተለያዩ አልባሳትን፣ 25 ተሽከርካሪ የእንስሳት መኖን፣ 716 ኩንታል የምግብ ድጋፍን፣ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ፍራሽና ብርድልብስን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በጥሬ ገንዘብ የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍን ያካተተ መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ እና የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ገልፀዋል።

ድጋፍን የተረከቡት የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተለይም የእንስሳት መኖ ድጋፉ በዚህ ወቅት የበለጠ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ሌሎች አካላትም የድርቁን ስፋት በመረዳት የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version