አዲስ አበባ፣የካቲት 24፣2014 (ኤፍ ቢሲ) “ግብርናችንን በማዘመን ምርትና ምርታማነታችንን ካላሳደግን ከድህነት መውጣት አንችልም” አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ።
በክልሉ የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂን በስፋት ጥቅም ላይ ማዋል በሚቻልበት ዙሪያ ላይ ያተኮረ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የተገኙት ዶ/ር ይልቃል፥ ከድህነት መውጫ ዋናው መንገድ ግብርና መሆኑን በማንሳት ለአርሶ አደሩ ብድር በማመቻቸትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሃ/ማርያም ከፍያለው በዚህ ወቅት እንደገለፁት፥ የአማራ ክልል የሀገሪቱን አመታዊ የምርት መጠን 33% እንዲሁም በመሬት ሽፋን 35% ይዞ የግብርና ሜካናይዜሽን አተገባበሩ ግን ዝቅተኛ ነው።
ክልሉ 4 ነጥብ 9 ሚሊየን ሄክታር ለእርሻ የሚሆን መሬት ያለው ቢሆንም፥ የአርሶ አደሩ አስተራረስ ግን አብዛኛው ባህላዊ በመሆኑ በቂ ምርት ማግኘት አልተቻለም ሲሉም ተናግረዋል።
ለችግሩ እንደ ዋነኛ ምክንያት የሚጠቀሱት ደግሞ የሜካናይዜሽን ተቋማት በቅርብ አለመኖር፣ የባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ አለመስራት፣ የፋይናንስ አቅርቦትና የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደሆኑ የቢሮ ሀላፊው ገልፀዋል።
ይህንን ችግር ለመቅረፍ ደግሞ የጋራ ጥረት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
በሙሉጌታ ደሴ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

