Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኮልፌ አጠና ተራ ታይዋን አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታዉ ኮልፌ አጠና ተራ ታይዋን አካባቢ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
ትላንት ምሽት 4:21 በደረሰው የእሳት አደጋ ሁለት የእሳት አደጋ ሰራተኞች በጭስ የመታፈን ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
የአደጋዉ ጥሪ እንደደረሰ 13 የእሳት ማጥፊያ ተሽካርካሪዎች እና 87 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቦታው ተገኝተው አደጋው ከዚህ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል መቆጣጠር ተችሏል፡፡
በተደረገዉ ርብርብም 50 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት ማዳን መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ሞላ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡
የንግድ ሱቆቹ በቀላሉ ሊቀጣጠል ከሚችል ቆርቆሮ ና ከእንጨት መሰራታቸዉ፣ የኤሌክትሪክ መስመር ፈጥኖ አለመቋረጡ እና የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች መግቢያ መንገድ አለመኖር ለእሳት አደጋዉ መባባስ ምንያት መሆኑንም ነው ጨምረው የገለጹት፡፡
በኮልፌ አጠና ተራ በሚገኙ የገበያ ማዕከላት ተደጋጋሚ የእሳት አደጋ ከሚያጋጥማቸዉ ገበያ ማዕከላት አንዱ መሆኑም ተጠቅሷል።
በገበያ ማዕከል ስፍራዎች አካባቢ ስራ ላይ ያሉ አካላት ሱቆቻቸዉን ዘግተዉ በሚሄዱበት ጊዜ÷ የኤሌክትሪክ መስመሮችን ማቋረጥ፣ ለእሳት አደጋ ምክንያት የሚሆኑ አሰራሮችን ማስወገድ፣ አጠራጣሪ ሁኔታዎችን በትኩረት መከታተል እና ቅድመ ጥንቃቄዉ ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግም ተገልጿል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version