Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሩሲያ እና ዩክሬን ሰብአዊ መተላለፊያ መስመር ለማዘጋጀት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለቱ ሀገራት ትናንት በቤላሩስ ባደረጉት ሁለተኛ ዙር ድርድር ንጹሃን ከጦርነቱ ቀጠና እንዲወጡ የሚያስችል ሰብአዊ መተላለፊያ መስመር ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል።
በዚህም ንጹሃንን ከጦርነት ቀጠና ለማስወጣት እና የሰብአዊ እርዳታ እንዲያገኙ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የዩክሬን ፕሬዚዳንት አማካሪ ማይካሂሎ ፖዶሊያክ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።
ንጹሃንን ከጦርነቱ ጉዳት ለማዳን ብቻ መንገዱ ክፍት ነው ሲሉ ፖዶሊያክ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አረጋግጠዋል፡፡
ትናንት በተካሄደው ድርድር÷ ሁለቱ ወገኖች በወታደራዊ እና ሰብአዊ ጉዳዮች እንዲሁም ለግጭቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ መስጠት በሚቻልበት አግባብ ላይ መምከራቸውን የሩሲያ ልዑካን ቡድን መሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ ተናግረዋል፡፡
በድርድሩ ወቅት በተወያዩባቸው አንዳንድ ነጥቦች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት የቡድን መሪው በሰብአዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግባባት ላይ መደረሱ ትልቅ እድገት ነውም ብለዋል፡፡
የሶስተኛው ዙር የሰላም ድርድር በቅርቡ ሊካሄድ እንደሚችል መገለጹንም ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version