አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመብራት እና ቴክኒካል መተላለፍያ የኬብል መስመሮች ላይ ስርቆት በመፈጸሙ ተቋርጦ የነበረው የአዲስ አበባ ባቡር የትራንስፖርት አገልግሎት በከፊል መጀመሩ ተገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት የትራንስፖርት ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ሂጲሶ ለፋና ብርድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ከካሜራ እይታ ውጭ በሆኑ የመብራት እና ቴክኒካል መተላለፍያ የኬብል መስመሮች ላይ ስርቆት በመፈጸሙ ተቋርጦ የቆየው የባቡር የትራንስፖርት አገልግሎት ዛሬ በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
በዚህም ከቃሊቲ እስከ መሿለኪያ ባለው መስመር አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጸው፥ በቀጣይ በሌሎች መስመሮችም ሙሉ በሙሉ ስራ ለማስጀመር ድርጅቱ በሙሉ አቅሙ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኬብል ስርቆቱ የተፈጸመው ስባተኛ ፣ ልደታ እና ሐያት አካባቢ እንደሆነም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
አገልግሎቱ በመቋረጡ ምክንያት በቀን ከ350 ሺህ ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ እንዳልተቻለም አስታውቀዋል፡፡
በሲሳይ ጌትነት
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

