Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ10 ሺህ በላይ መደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎቹን መጋቢት 12 እና 13 ይቀበላል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ10 ሺህ በላይ መደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎቹን መጋቢት 12 እና 13 እንደሚቀበል አስታወቀ፡፡

በአሸባሪው ቡድኑ ህወሓት ውድመት ከደረሰበት በኋላ መደበኛ ሰራውን በመጀመር ዝግጅቱን ያጠናቀቀው ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሰራውን በመቀጠል አንደኛ አመትን ጨምሮ ተማሪዎቹን ከመጋቢት 12 ጀምሮ እንደሚቀበል ገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሀላፊ ዶ/ር ብርሀን አሰፍ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተቋሙ ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ለተማሪዎች ጥሪ ማድረጉን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከ1ኛ እሰከ 3ኛ ድግሪ ድረስ ያሉ ተማሪዎችን እንደሚቀበል የተገለጸ ሲሆን÷ በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሚማሩ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ሁሉም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችም በተጠቀሰው ቀን በዩኒቨርሲቲው በመገኘት ምዝገባ ማካሄድ እንዳለባቸው አሳስቧል።

ዩኒቨርሲቲው በአሸባሪው ቡድን ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ውድመት እንደደረሰበት ይታወቃል።

በከድር መሀመድ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version