Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ104 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 104 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉሙሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹ ባደረገው ክትትል÷ 100 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች እና 3 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ይዟል፡፡
የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት አዋሽ፣ ሐዋሳ እና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
63 ነጥብ 5 ሚሊየን አዋሽ፣ 6 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ሀዋሳ እና ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል ተብሏል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻና በጥቆማ የተያዙ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ከኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታልም ነው የተባለው፡፡
ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪ ማቅረቡን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version