አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው የሚኒስትሮች የልዑካን ቡድን ጅግጅጋ ከተማ ገባ፡፡
የልዑካን ቡድኑ ጅግጅጋ ከተማ ገራድ ዊል ዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በሶማሌ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማንና በክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል።
ወደ ክልሉ የገባው የልዑካን ቡድን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ መሀመድ ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ፣ የአለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ዋና ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን እንዲሁም የአፍሪካ ልማት ባንክ ተወካይ አቶ አብዱል ካማራ ያካተተ ነው።
የልዑካን ቡድኑ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ከክልሉ ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

