Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ዐረፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ዐረፉ።

ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ዐርፈዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፥ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትን ከመምራታቸው በተጨማሪ ቀደም ብለው በአርሲ እና በመቐለ አህጉረ ስብከት ተመድበው አገልግለዋል።

Exit mobile version