Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሲዳማ ክልል በየዓመቱ የሚዘጋጀው የአምራች ኢንዱስትሪዎች ዐውደ ርዕይና ባዛር ዛሬ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በየአመቱ
የሚያዘጋጀው የአምራች ኢንዱስትሪዎች አውደ ርዕይ እና ባዛር በዛሬው ዕለት “እኔ የሀገሬን ምርት እጠቀማለሁ” በሚል መሪ ቃል በሐዋሳ በይፋ ተከፍቷል።
የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀምበረ÷ እንደክልል ከ840 በላይ አምራቾች እንደሚገኙ እና በግብርና ላይ ጥገኛ የሆነውን ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ በማሸጋገርና ግብርናን በማዘመን የገበያ መረጋጋትና ትርፋማነትን ማምጣት የባዛሩ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችም ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት የአቅርቦት እጥረት መቅረፍና የውጭ ኢኮኖሚ ጥገኝነትን ሊያስቀር የሚችል አቅም መፍጠር ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ ዩስፍ÷ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የኢኮኖሚ ሚናቸው ቀላል ባለመሆኑ አምራች ኢንዱስሪዎችን ማበረታታት ይገባል ብለዋል፡፡
አምራቾችም የሚያመርቱትን ምርት በጥራትና በብቃት በማምረት ምርቶቻቸው ይበልጥ በማስፋት ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ገበያ ማስተሳሰር ያስፈልጋል ማለታቸውን ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version