Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በኢትዮጵያ ስልጠና እየወሰዱ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ማሠልጠኛ ተቋም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ግጭቶችን አስቀድሞ መከላከል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

በሥልጠናው ኢትዮጵያን ጨምሮ ከቡሩንዲ፣ ኡጋንዳ እና ሶማሊያ የተውጣጡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እየተሳተፉ ነው።
ከጃፓንና ከተባበሩት መንግስታት ጋር በመተባበር የሚሰጠው ስልጠና÷ በቀጠናው ሀገራት የሚፈጠሩ የሠላም መደፍረስ ችግሮችን ለማስቆም ያግዛል ነው የተባለው፡፡

ጦርነት በሠው ልጆች ላይ የሚያስከትለው መዘዝ ከፍተኛ በመሆኑ ግጭቶችን አስቀድሞ ለመከላከልና ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ከሁሉም ተባባሪ ሀገራት ጋር እየተሠራ መሆኑን የዓለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ማሰልጠኛ ተቋም አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ሰብስቤ ዱባ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አንዷ መሥራች ሀገርና በህብረቱም ብዙ ቁጥር ያለው ጦሯን ለሠላም ማስከበር ተልዕኮ እየላከች ያለች ሀገር መሆኗን የገለጹት ደግሞ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ናቸው፡፡

የዓለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ማሠልጠኛ ትምህር ቤት ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጌቱ ታዬ በበኩላቸው÷ ሠልጣኞች የተባበሩት መንግስታትን ተልዕኮ ተቀብለው ከመሠማራታቸው በፊት ስለ ግጭት መከላከል ግንዛቤ ከመፍጠር አንፃር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version