Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ በቡድን በመደራጀት እና በተናጠል ተሽከርካሪዎችን ሲሰርቁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡድን በመደራጀት እና በተናጠል ተሽከርካሪዎችን ሲሰርቁ እና ሲተባበሩ የነበሩ 21 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
የተሰረቁ ተሽከርካሪዎችን ማስመለሱንም ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀሙ የተሽከርካሪ ስርቆቶችን እና ለህብረተሰቡ ስጋት የሆኑ ወንጀሎችን ለመከላከል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቅሷል።

የመኪና ስርቆትን ለማስቆም እና ፈፃሚያቸውን ለመያዝ የልዩ ልዩ እና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ከክትትል ክፍሉ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ጥረት በሶስት ቡድን የተደራጁ 16 ተጠርጣሪዎችን እና በተናጠል የመኪና ስርቆት ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 5 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ነው ያለው።

በአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዚዩን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ያሬድ አለማየሁ፥ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተከናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ ቀደም ሲል ፈፃሚያቸው ባልታወቀ የተመዘገቡ ወንጀሎች በእነዚህ ተጠርጣሪዎች እንደተፈፀሙ በማረጋገጥ የተሰረቁትን ተሽከርካሪዎች ማስመለስ ተችሏል ብለዋል።

በዚህም በተለያየ ጊዜ የተሰረቁ ከሚኒባስ እስከ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ለባለንብረቶቹ ማስመለስ መቻሉን ጠቅሰው፥ የተወሰኑ ተሽከርካሪዎች የውስጥ እቃዎቻቸው ተሸጦ መገኘታቸውንም አስረድተዋል።

አሁን ላይም ተጠርጣሪዎቹ በ10 መዝገቦች ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።

የተሽከርካሪ ባለንብረቶችም አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version