Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደቡብ አፍሪካ ኤ ኤን ሲ ፓርቲ ተወካዮች በብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ለመታደም አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ “የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ”) ፓርቲ ተወካዮች በብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለመታደም ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።

የፓርቲው ብሔራዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ፕሮፌሰር ኢቅባል ጃዝብሃይ እና የፓርቲው ዋና ሥራ አስኪያጅ ፌቤ ፖትጌተር ናቸው አዲስ አበባ የገቡት።

እንግዶቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አምባሳደር ሐሰን አብዱልቃድር በርከት አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል።

የደቡብ አፍሪካው ኤ ኤን ሲ ከተመሠረተ 110 ዓመት የሞላው ሲሆን 108ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ሲያከብር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተገኝተው መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version