Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከሳፋሪኮም ጋር የኦፕቲካል ፋይበር መስመር ኪራይ ሥምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር ሁለቱ ተቋማት በጋራ ተባብረው እንዲሰሩ መሠረት የሚያስችል የኦፕቲካል ፋይበር ኪራይ ስምምነት ተፈራረመ።
 
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር አንዋር ሶውሳ ናቸው የተፈራረሙት፡፡
 
ስምምነቱ በመጀመሪያ ምዕራፍ 4097 ኪሎ ሜት፣ በሁለተኛው ምዕራፍ 2078 ኪሎ ሜትር እንዲሁም በሶስተኛው ምዕራፍ 2904 ኪሎ ሜትር የኦፕቲካል ፋይበር መስመር ኪራይን እንደሚጠቃልል ተገልጿል፡፡
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት÷ ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ተባብረው እንዲሰሩ መሠረት የሚጥል ነው፡፡
 
ተቋሙ ከኃይል ማመንጨት እና ማስተላለፍ ባሻገር የቴሌኮም ዘርፉን ዲጂታል ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡
 
ሥምምነቱ ለሳፋሪኮም እንደ መልካም ጅማሮ የሚታይ ነው ያሉት አቶ አሸብር÷ የጋራ ተጠቃሚነትን ከፍ የሚያደርግ በመሆኑ ትልቅ ዕድል ነው ብለዋል፡፡
 
የሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር አንዋር ሶውሳ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ እያሳየች ያለውን አዎንታዊ ዕድገት አድንቀው ሥምምነቱ ከተቋሙ ጋር ያለንን በጋራ የመሥራት ፍላጎት የሚያጠናክር ነው ብለዋል፡፡
 
ኩባንያቸው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑን ለማሳካት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
 
ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ የቴሌኮም አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለማቅረብም እየተሰራ መሆኑን መግለጻቸውንም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነወ መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version