Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በብሔራዊ መታወቂያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ”አንድ ሰው አንድ ነው” በሚል መሪ ሃሳብ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም በዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ÷ የብሔራዊ መታወቂያ በቀጣይ በሀገሪቱ ከመታወቂያ እና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን እንዴት ማቃለል እንደሚችል እና አስፈላጊነቱ ምን ያህል እንደሆነ ተገልጿል።
በተለይም ከመታወቂያ ጋር ተያይዞ አንድ ሰው ብዙ ማንነት እንዳለው እየታየ መሆኑና በብዙ ማንነቱ የተለያዩ ችግሮችን እየፈጠረ ይስተዋላል ተብሏል። ይህም በአገልግሎት ሰጪዎች ላይ እምነት እንዲያጡ እያደረገ ነው ተብሏ፡፡
የዲጂታል መታወቂያ እነዚህን ችግሮች የሚቀርፍ እና አንድ ሰው አንድ ማንነት ብቻ እንዲኖረው የሚያደርግ በመሆኑ አስፈላጊነቱ ከፍኛ ነው ተብሏል፡፡
በዚህ ውይይትም ወደ ስራ ከተገባ አንድ አመት ተኩል የሆነውን የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም በቀጣይ የሚጨመሩ እና የሚቀነሱ ነገሮች ላይ እና በረቂቅ አዋጁ ላይ ከህዝብ፣ ከመንግስትና ከተለያዩ ተቋማት አስተያየት ይሰበሰባል ነው የተባለው።

በአፈወርቅ አለሙ እና በተስፋዬ ከበደ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version