Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አየር መንገዱ በአስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት ወደ ባሕር ዳር የሚያደርገውን በረራ ሰረዘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት ወደ ባሕር ዳር የሚያደርገውን በረራ መሰረዙን አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ሥራ አስኪያጅ ተስፋዬ ቀለሙ እንደገለጹት ከመጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ በተከሰተ አቧራ መሰል ጭጋግ ምክንያት መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም ሊደረጉ የነበሩ 11 በረራዎች ተሰርዘዋል።
እንዲህ አይነቱ ክስተት ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ ወር ተከስቶ እንደነበር አስታውሰው÷ የአየር ሁኔታው እንደተስተካከለ የበረራ አገልግሎቱ እንደሚቀጥልም ነው አቶ ተስፋዬ የተናገሩት።
ክስተቱ ዛሬ 11:00 ላይ በጎንደርም ያጋጠመ ቢሆንም የአየር ሁኔታው በመስተካከሉ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ሥራ አስኪያጁ ለአሚኮ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version