አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ለብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች መልካም የሥራ ጊዜ እንዲሆን ተመኙ፡፡
ርዕሰ መስተዳደሩ÷ ብልፅግና ፓርቲ እያካሄደው በሚገኘው የፓርቲው የመጀመሪያ ጉባኤ ላይ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የፓርቲው ፕሬዚዳንት እንዲሁም አቶ አደም ፋራህ እና አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
“በሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ህዝብ ስም መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ” ብለዋል።
̋ከቆራጥና ለህዝብ ከቆሙ መሪዎቻችን ጋር በመሆን ሀገራችንን እናሻግራለን የኢትዮጵያ ብልፅግና እናረጋግጣለን“ ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

