አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ማሳተፍ የሚችል ሆኖ መጽደቁን የፓርቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ገለጹ።
ዶክተር ቢቂላ የፓርቲው አንደኛ ጉባኤ የዛሬ ከሰዓት በኋላ ውሎውን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው እንዳመለከቱት ጉባኤው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ማጽደቅ፣ የፓርቲውን ፕሮግራም እና የፓርቲውን ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ምርጫ ማካሄዱን አመላክተዋል።
መተዳደሪያ ደንቡ ፓርቲው ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ማሳተፍ የሚችል ሆኖ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ህብረ ብሔራዊ ፓርቲና ዴሞክራሲን፣ አሳታፊነትንና አካታችነትን ለመለማመድ በሚያስችል ሁኔታ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
የፓርቲው ፕሮግራም በጉባኤው ውይይት ተደርጎበት መጽደቁን የገለጹት ዶክተር ቢቂላ፥ ፕሮግራሙ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚረዱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ጉዳይ፣ የውጭ ጉዳይና የዲፕሎማሲ ጉዳዮችን የያዘ መሆኑን አብራርተዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

