አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና አሜሪካ ከሩሲያ እና ዩክሬን ቀውስ ጋር በተያያዘ ሀሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጨችነው ስትል ኮነነች፡፡
ዋሺንግተን ሩሲያ የጦር መሳሪያ እርዳታ ጥያቄ ለቻይና አቅርባለች ማለቷ ይታወሳል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷ አሜሪካ ከሩሲያ እና ዩክሬን ቀውስ ጋር በተያያዘ ሀሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጨች ነው ሲሉ ኮንነዋል፡፡
የዋሽንግተን ባለስልጣናት ሩሲያ ከቻይና የጦር መሳሪያ እርዳታ ጥያቄ አቅርባለች በሚል የሚሰራጩትን መረጃም መሰረተ ቢስ ውንጀላ ሲሉ አጣጥለዋል፡፡
አሁን ላይ አሳሳቢው ጉዳይ በዩክሬን የተፈጠረውን ቀውስ ማርገብ ነው ብለዋል።
አያይዘውም በእሳት ላይ ነዳጅ እየጨመሩ ውጥረቱን ማባባስ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው ማለታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

