አዲስ አበባ፣መጋቢት 5፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን አገሮች ድርጅት ( ኔቶ) በዩክሬን ግጭት ውስጥ ከገባ 3ኛው የዓለም ጦርነት ተጀመረ እንደማለት ነው ሲሉ የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ቻርለስ ሚሼል ተናገሩ፡፡
የኅብረቱ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዛሬ ለንባብ ለበቃው ኤል ፔስ የተሰኘ የስፔን ታዋቂ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ፥ የአውሮፓ አገሮች በዩክሬን እና ሩሲያ ግጭት ውስጥ መግባት የለባቸውም ብለዋል፡፡
የምዕራባውያን አገሮች በሞስኮ እና በኪዬቭ መካከል ባለው ግጭት ውስጥ ጣልቃ መግባት የለባቸውም ያሉት ፕሬዚዳንቱ በሩስያ እና በኔቶ መካከል ግጭት ከተፈጠረ ደግሞ የዓለም የኒውክሌር ጦርነት ተጀመረ ማለት ነው ሲሉ ነው ያብራሩት።
ፕሬዚዳንቱ በፈረንሳይ የተካሄደውን የአውሮፓ ኅብረት ስብስባን ባሰጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ከተከሰተው የዩክሬን ግጭት ጀርባ ውስብስብ ችግሮች መኖራቸውን ጠቅሰው፥ ሰላማዊ ውይይቱ በጥንቃቄ እንዲካሄድ አሳስበዋል፡፡
ቀደም ሲል የቤልጅየም ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ቻርለስ ሚሼል ለጋዜጣው እንደተናገሩት፥ ሩሲያ የኒውክሌር ባለቤት ነች፣ እናም በኔቶ እና በሩሲያ መካከል ያለው ውጥረት ወደ ግጭት ከተቀየረ ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እንደምንገባ ጠንቅቀን እናውቃለን ነው ያሉት፡፡
ለዚህ ግጭት ዋነኛው መፍትሄ ምክክርና ውይይት ነው ያሉት የኅብረቱ ፕሬዚዳንት፥ አውሮፓ የአስታራቂነት ሚናዋን ለሌላ ለየትኛውም ኃይል – ለአሜሪካም ሆነ ለቻይና – አሳልፋ መስጠት የለባትም ብለዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

